የጥምቀት በዓል በሊድስ
Jan 19, 2025 at 04:20 PM
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ነገ ጥር10 እና እሁድ11/2017 (January18-19 /2025) የዘንድሮን 2017 ዓምየጥምቀት በዓልን በደብራችን በሊድስ ደብረ ስብሐት መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን የደብረ ደብረ ፀሀይቅድስት ኪዳነ ምህረት የደብረ ፀሀይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጋራ በመሆን በታላቅ ድምቀት ይከበራል::
ነገ ቅዳሜ ጥር 10/2017 (Jan 18/2025 ) ከሰባቱ አጿማት አንዱ ፆመ ገሀድ መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም በግዴታ የምንፆመው መሆኑን እንድታውቁ እያሳሰብን
የከተራ መርሀግብሩ የሚጀምረዉ 4;30pm ሲሆን የሌሊቱ ማህሌት 12:00 ;Midnight )ይጀመራል፤ ቅዳሴ 4;30 am ሥርዓተ ጥምቀቱ የቅዳሴው ፀሎት እንደተጠናቀቀ ይከናወናል::
መልካም በአል
የደብሩ ጽሕፈት ቤት