የጌታችን ልደት በአል
Jan 19, 2025 at 04:18 PM
በሊድስና አካባቢው የምትኖሩ ምእመናን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልን።
እንደሚታወቀው የፊታችን እሁድ ጥር4/2017 (Jan12/2025) ሰንበት ትምህርት ቤታችን የጌታችንን ልደት ምክኒያት በማድረግ በስብከተ ወንጌልና በዝማሬ ለማሳለፍ መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል::
በመሆኑም መርሀ ግብሩን በጊዜ ለማጠናቀቅ ይረዳን ዘንድ ቅዳሴ የሚጀመረው ከጠዋቱ 6:00am ስለሆነ በጊዜ እንድትመጡ እያሳሰብን
የገናን ፆም ምክንያት በማድረግ ለእግዚአብሔር ቤት የገና ስጦታ እንድናጠራቅምበት የወሰዳችሁትን የገንዘብ ማጠራቀሚያ ይዛችሁ በመምጣት ለፅህፈት ቤት እንድታስረክቡ በትህትና እንጠይቃለን::
የደብሩ ሰበካ ፅህፈት ቤት